Tuesday, May 6, 2014


አባ ዱላ ገመዳ ስለኦሮሚያ ተማሪዎችና ጥያቄዎቻቸው ለቪኦኤ መግለጫ ሰጡ

የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ “ተቃውሞ ያሰሙ አንዳንድ የኦሮሞ ተማሪዎች በመንግሥት ኃይሎች መገደላቸው ስህተት ነው” አሉ።


አፈ ጉባዔው ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተቃዋሚዎቹ ተገቢ ጥያቄ እንዳነሱ ጠቅሰው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግም ሕገ-መንግሥታዊ መብት መሆኑን የጠቀሱት አባዱላ ተማሪዎቹ ግን ሠልፍ ለማድረግ መንግሥት የሚጠይቀውን መስፈርት አላሟሉም ብለዋል።

“በተለይም ብዙ ሰዎች በተገደሉበት በአምቦ ከተማ ተማሪዎች ያልሆኑ ያሏቸው ሰልፉን በመቀላቀል ንብረት በማውደማቸው መንግሥት እርምጃ ለመውሰድ ተገድዷል” ብለዋል፡፡

Thursday, May 1, 2014

ጭፍጨፋውና አፈናው ይቁም!!!


ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲንቅናቄ፣ ዘረኛው ወያኔ በኦሮሚያ ሕዝብና ወጣቶች ላይ እያካሄደው ያለውን አረመኔያዊ ጭፍጨፋ፣ እስርና አፈናን በጥብቅ ይቃወማል። ህወሓት፣ ኦህዴድ እና በዚህ ጭፍጨፋ እጃቸው ያለበት ሁሉ ከተጠያቂነት የማያመልጡ መሆኑን ያስገነዝባል።
የአሮሚያ ወጣቶች በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ስም የድሀ ገበሬዎች መፈናቀልን መቃወማቸው ፍትሀዊ ነው። የወያኔ “ማስተር ፕላኖች” የወያኔ የዘረፋ እቅዶች መሆናቸው በተደጋጋሚ የታየ ጉዳይ ነው። ነዋሪዎቹን ያላማከረ፣ ግንባር ቀደም ባለጉዳዮችን ባለቤት ያላደረገ፣ የሕዝብ ይሁንታ ያላገኘ ማስተር ፕላን ተፈፃሚ ማድረግ አይቻልም።
ወያኔ ኦሮሚያን ብቻ ሳይሆን መላዋን ኢትዮጵያ በምስለኔዎቹ አማካይነት እየገዛ የኢትዮጵያን ውድ ልጆች በራሳቸው ጉዳይ ባይተዋር አድርጓቸዋል። ኦህዴድ በወያኔ ቅጥረኛነት የኦሮሚያ ወጣቶችን በማስጨፍጨፍ ላይ ያለ እኩይ የአድርባዮች ስብስብ ነው።  ወጣቶች የተቃወሙት ይህንን ነው።እነዚህ ወጣቶች በአካባቢያቸው ጉዳይ ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባቸዋል። ድምፃቸው ሊሰማ ይገባል። የሌላው አካባቢም ወጣት የኦሮሚያ ገበሬ መፈናቀል ያገባዋል። ኢትዮጵያዊያን በኢትዮጵያ ውስጥ በሚደረግ ጉዳይ ሁሉ ያገባናል። በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል ውስጥ ወያኔ የራሱን እቅድ እንዲጭንብን አንፈልግም።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ወጣቶች ጥያቄ የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ጥያቄ አድርጎ እንዲወስድ ጥሪ ያደርጋል።  በጉራፈርዳና በቤንሻንጉል የተጀመረው መፈናቀል ዛሬ አዲስ አበባ አጎራባች ከተሞች ደርሷል። በአምቦ ይህንን የተቃወሙ ወጣቶች በግፍ ተጨፍጭፈዋል፤ በሌሎች ቦታዎችም ላይ ግድያውና እስሩ በርትቷል። ወጣቱ  የጥይት እራት ሆኖ እስኪያልቅ መጠበቅ አንችልም፤ ሁሉም ትግሉን ይቀላቀል።
የወያኔ የጥቃት ሰለባ የሆኑት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይን ያነሱ ወጣቶች ብቻ  አይደሉም። በአንድ ወይም በሌላ መንገድ የወያኔን አምባገንነት የተቃወሙ በሙሉ የጥቃቱ ሰላባዎች ናቸው። ለሰልፍ ቅስቀሳ አደረጋችሁ በሚል የታሰሩ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ሰልፉ ተደርጎ  ካለቀ በኋላም አልተፈቱም።  ይህ ሰቆቃ ማብቃት አለበት።
ጭፍጨፋውና አፈናው ይቁም!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!

ተጨማሪ መረጃዎች በህገ ወጡ መጅሊስ መፈንቅለ ስልጣን ዙሪያ!


ድምፃችን ይሰማ 


ሐሙስ ሚያዝያ 23/2006

በትናንቱ ሰበር ዜና በህገ ወጡ የፌደራል መጅሊስ ውስጥ የተደረገው መፈንቅለ ስልጣን ፕሬዝዳንቱን እስከማባረር መድረሱን ለማየት ተሞክሯል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን እነሆ!

የውዝግቡ ምንጭ በየካቲት አጋማሽ በድሬዳዋ ከተማ ላይ በተደረገው 11ኛው የመጅሊስ ጠቅላይ ጉባዔ ላይ የተሰጠው የአቋም መግለጫ ሲሆን በአቋም መግለጫው ላይ የተካተቱት አንዳንድ ነጥቦች መጅሊሱ ውስጥ ‹‹ለዘብተኛ›› አቋም የያዘውን ቡድን ለማግለልና ለማባረር ያቀዱ መሆናቸውም ተቃውሞ አስነስቷል፡፡

የአቋም መግለጫው መንስኤ መንግስት ከህዝበ ሙስሊሙ ፍላጎት ውጭ በመስከረም 27/2005 በቀበሌዎች ባካሄደው ህገ ወጥ የመጅሊስ ምርጫ ወደስልጣን ያመጣቸው አካላት ሁሉም በእኩል ደረጃ ጸረ-ሙስሊም አጀንዳውን ሊያስፈጽሙለት ባለመቻላቸው አካሄዱን እየተቃወሙት ያሉትን የአመራር አባላት ለማስወገድ ያለው ፍላጎት ነው፡፡ በአቋም መግለጫው ላይ በተካተቱት ነጥቦች መሰረት በተለይ መጅሊሱ በክልል ደረጃ ባለው ስልጣን የስራ አስፈጻሚ አባላቱን ውክልና ማንሳት እንዲችል መደረጉ (ነጥብ 4) ከመተዳደሪያ ደንቡ ጋር በግልጽ የሚጋጭ ሲሆን ይህም ‹‹እንዲወገዱ የፈለጋቸውን ሰዎች ያለ ህጋዊ ሂደት ማባረር እንዲችል መንገድ ይከፍታል›› የሚል ተቃውሞ እንዲነሳበት አድርጓል፡፡ ይህ ደግሞ በአቋም መግለጫው 1፣ 3፣ 4፣ 5 እና 10ኛ ተራ ቁጥሮች ላይ የተንጸባረቁት ሌሎች ነጥቦች፣ ማለትም አመራሩ ራሱን ከ‹‹አክራሪ››፣ ‹‹ወሐቢያ››፣ ‹‹ኢኽዋን›› እና ‹‹ተክፊር›› ማጥራትና ‹‹ጽንፈኞችን›› ማባረር እንዳለበት ከተቀመጠው ነጥብ ጋር ተዳምሮ መንግጅሊሱ ለሚያስፈጽመው የመንግስት እኩይ አጀንዳ እንቅፋት ሊሆኑ የሚችሉ አካላትን የማስወገድ መብት ይሰጠዋል ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ይህ ‹‹መጅሊሱ ሁሉንም አስተሳሰቦች አቻችሎ ቢሄድ ነው የሚሻለው›› የሚል አቋም ያራመዱትንና በትናንትናው እለት መፈንቅለ ስልጣን የተደረገባቸውን አባላት ከአክራሪው መፍቅሬ-አህባሽ ቡድን ጋር ካወዛገቡት ነጥቦች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡

ሌላው በአቋም መግለጫው ላይ መካተቱ የውዝግብ ምንጭ ያደረገው ነጥብ ደግሞ ከመንግጅሊሱ ቀጣይ እንቅስቃሴና አህባሽን አስገድዶ የመጫን ሂደት ጋር ተያይዞ የተያዘው አቋም ሲሆን ለዘብተኛው የአመራር ቡድን ‹‹መጅሊሱ ዳግም የህዝበ ሙስሊሙን ተቃውሞ ሊያገረሹ ከሚችሉ አካሄዶች መቆጠብ አለበት›› የሚል አቋም በመጅሊሱ ውስጥ ማራመዱ ጥርስ አስነክሶበታል፡፡ ይህ ቁጥብነት ከፌደራል ጉዳዮች ቀጥተኛ ትእዛዝ ብቻ በመቀበል እየተንቀሳቀሱ ላሉት መፍቅሬ-አህባሽ ቡድኖችም ራስ ምታት ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም በተቋሙ ስም መንግስት ያሻውን እንዳይፈጽም እንቅፋት የሆኑበትን አካላት ሁሉ ካሁን ቀደም ለረጅም ጊዜ በመጅሊሱ ውስጥ ሲያደርገው እንደቆየው ‹‹ውክልና ማንሳት›› የምትባለውን ዘዴ በመጠቀም ‹‹ለዘብተኞቹን›› ከጨዋታ ውጭ አድርጓቸዋል፡፡ በመጅሊሱ ታሪክ በአጋጣሚም ሆነ ባለማወቅ ከመንግስት ቁጥጥር ወይም ፍላጎት ውጭ በመጅሊሱ መዋቅር ውስጥ የገቡ አካላት፣ አልያም በመንግስት ፍላጎት ገብተው ኋላ ላይ ከመንግስት የተለየ አቋም ሲያራምዱ የተገኙ አመራር አባላት ሲወገዱ የነበረው በዚሁ ዘዴ ነበር፡፡ ዛሬም ያንኑ ያረጀ ስልት ራሳቸው በቀበሌ የ‹‹ቅርጫ›› ሂደት መርጠው ባቋቋሙት ህገ ወጥ ካቢኔ ላይ ደግመውታል - ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዲሉ!

በጉዳዩ ላይ የህዝበ ሙስሊሙ አቋም ግልጽ ነው፤ ህዝበ ሙስሊሙ መሪዎቹን ራሱ መምረጥ ይፈልጋል! በመጅሊሱ ውስጥ ከህዝብ እውቅናና ፍላጎት ውጭ ጥሩም ሆነ መጥፎ፣ ለዘብተኛም ሆነ ጽንፈኛ መሪዎች መምጣታቸውን ያወግዛል! መረዎቹን መምረጥ ያበት ህዝበ ሙስሊሙ ራሱ ብቻ ነውና!

(ከታች በመፈንቅለ ስልጣኑ የተባረሩት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ሸኽ ኪያር ሸኽ ሙሀመድ አማን በድሬዳዋው ጉባዔ የጸደቀውን የአቋም መግለጫ ተቃውመው ለተለያዩ የመንግስት አካላት በመጋቢት 26 እና 29/2006 የጻፏቸው ሁለት ደብዳቤዎች እና በድሬዳዋው ጉባዔ የተላለፈውን የአቋም መግለጫ የሰፈረበት የፎቶ አልበም ተያይዟል)

https://www.facebook.com/media/set/?set=a.747502598634432.1073741858.324725940912102&type=3&uploaded=9

ትግላችን እስከድል ደጃፎች ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!
ህገ ወጥ መጅሊሱ የሚገኝበትን ሁኔታ አስመልክቶ ፕሬዝዳንቱ ሸኽ ኪያር የጻፉት ደብዳቤ Page 1 of 3

በኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ መካረ ስጋት ፈጥሯል

ኦህዴድ የተከፋፈለ አቋም ይዟል፤ ኢህአዴግ ጉልበት መርጧል!!

በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ድምጽ ለማሰማት በሞከሩና ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ሰልፍ በወጡ ወገኖች ላይ አገዛዙ የ”ከፋ” ነው የተባለ ሃይል መጠቀሙ ተሰማ። ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ታስረዋል። ለተቃውሞ መነሻ በሆነው አዲሱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ ኦህአዴድ ተመሳሳይ አቋም መያዝ አልቻለም። ችግሩን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ያልቻለው ኢህአዴግ ጉልበት መምረጡ አገሪቱ ውስጥ ካለው የተከማቸ ብሶቶች ጋር ተዳምሮ አለመረጋጋቱን ያሰፋዋል የሚል ስጋት አለ።
ከኦሮሚያ ክልል አስተዳደር የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት በአቀራረቡ ቢለያይም ከተለያዩ ሚዲያዎች የሚሰሙት ዜናዎች ሊስተባበሉ የሚችሉ አይደሉም። በታችኛው እርከን የሚገኙትን ጨምሮ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በጥቅሉ፣ ገሃድ አይውጣ እንጂ በመዋቅር ውስጥ ያሉ ሰራተኞችና ካድሬዎች የተቃውሞው ተሳታፊና ደጋፊ መሆናቸውን ክልሉም ሆነ ኢህአዴግ አረጋግጠዋል።
demoየአዲስ አበባ አዲሱ ማስተር ፕላን በዙሪያዋ ያሉትን ስድስት የኦሮሚያን ከተሞችና ስድስት የገጠር ቀበሌዎች የተካተቱበት መሆኑ ያስነሳው ተቃውሞ ቀደም ሲል በክልሉ በምክር ቤት ደረጀ በካድሬዎች ተቃውሞ አጋጠመው። ይህንኑ ተከትሎ ከሳምንት በፊት በአንዳንድ የትምህርት ተቋማት ብልጭ ድርግም ሲል የነበረው ተቃውሞ እየጠነከረ መጣ። የክልሉ የጎልጉል ምንጭ “ተቃውሞው እንደሚጨምር፣ ካድሬውም የተቃውሞው ስውር አጋር እንደሆነ፣ በመረጃ ትንተና አስቀድሞ ይታወቅ ነበር። በዚሁ መሰረት አስቀድሞ አመጹን ማምከን ካልተቻለ የማያዳግም ርምጃ እንዲወሰድ ለፌዴራልና ለመከላከያ አባላት መመሪያ ተሰጥቷል”።
የሰላማዊ ሰልፍ በሚጀመርበት አካባቢ ሌላውን “ሊያስተምር” የሚችል ከበድ ያለ የሃይል ርምጃ እንዲወሰድ በተላለፈው መመሪያ መሰረት ተግባራዊ ቢደረግም ረብሻውና የተቃውሞ እንቅስቃሴው እየሰፋ መሄዱን የጎልጉል መረጃ አቀባይ ይናገራሉ። ከከተማ ወደ ከተማ እየሰፋ የሄደው ተቃውሞ፣ የተቃውሞው አካል በሚመስሉ የስለላ ሰራተኞች በሚያቀብሉት መረጃ መሰረት ለማስታገስ ቢሞከርም አለመቻሉ ኢህአዴግ ውስጥ ጭንቀት ፈጥሯል።
የኦህዴድ አባላት በከፍተኛ አመራር ላይ ያሉትን ጨምሮ ተመሳሳይ አቋም ያልያዙበት አዲሱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጉዳይ በኦሮሚያ የተላዘበውን የፖለቲካ ችግር ሊያባብሰው ይችላል በሚል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኢህአዴግ የፖሊስ የመከላከያ ሃይላት ከልዩ መመሪያ ጋር በተጠንቀቅ እንደቆሙ ምንጩ አመልክተዋል። ይሁን እንጂ በኦህዴድ የታችኛው የቀበሌ መዋቅር ጭምር ተቃውሞው ስለሚደገፍ የአቋም መንሸራተት ሊፈጠር ይችላል የሚለው ስጋት ከፍተኛ መሆኑንንም አልሸሸጉም።
ከተለያዩ የማህበረሰብ አምዶች ሲደመጥ እንደሰነበተውና ሚያዚያ 22፤2006 (ኤፕሪል 30/2014) ቀን የአሜሪካ ሬዲዮ ከስፍራው ሰዎችን በማነጋገር እንደገለጸው ጅማ፣ አዳማ፣ ነቀምት፣ አምቦ፣ ሃሮማያ፣ ድሬዳዋ፣ በመሳሰሉት ከተሞችና የትምህርት ተቋማት ማህበረሰብ ላሰሙት የተቃውሞ ድምጽ የተሰጣቸው ምላሽ ዱላና እስር ነው። ከአምቦ በስልክ ስለሁኔታው የተናገሩ እንዳሉት አላፊ አግዳሚው ሳይቀር “ተጨፍጭፏል”።
በተጠቀሰው ቀን ረፋዱ ላይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ ከሰዓት በኋላ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለተቃውሞ ሲወጡ የመከላከያ አንጋቾችና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በወሰዱት የሃይል ርምጃ በርካቶች መቁሰላቸውን፣ በነፍስ አውጪኝ አጥር ዘለው የሸሹትን በማሳደድ ጨፍጭፈዋቸዋል። እኚሁ ሰው በስልክ እንደተናገሩት “ሸሽተው ወደ መኖሪያ ቤታቸው የመጡትን ተማሪዎች ለምን ቤትህ አስገባህ ተብዬ ተጨፈጨፍኩ፣ ነፍሴን ለማትረፍ መሬት እየተንከባለልኩ ጮህኩ። ሁለት ልጆቼን ወሰዱ” በማለት ሃዘናቸውን ገልጸዋል። የአምቦ ቤተመንግሥትም እስረኛ እንደሞላው አመልክተዋል።
ለማቅረብ ከያዟቸው ሶስት ጥያቄዎች መካከል አንዱ “ፊንፊኔ ያለው የአጼ ሚኒሊክ ሃውልት ይነሳ የሚል ነው” በማለት ፈርቶ እንደተሸሸገ የተናገረ ተማሪ ከአዳማ ለቪኦኤ ተናግሯል። የቪኦኤው ዘጋቢ ባለስልጣናትን ለማነጋገር ሞክሮ እንዳልተሳካለት፣ በመጨረሻም ከኦሮሚያ ምክር ቤት ያገናቸው ሰው መልስ ሳይመልሱ እንደመሳቅ እያሉ ስልኩን እንደዘጉት በግብር አሳይቷል።
ከምርጫ 97 በፊት አዳማን የኦሮሚያ ዋና ከተማ መደረጓን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ችግር ከምርጫ 97 በኋላ ቀውሱ እልባት እንደተበጀለት ይታወሳል። በወቅቱ በሜጫና ቱለማ ማህበር አስተባባሪነት አዲስ አበባ ላይ የተካረረ ሁኔታ ተፈጥሮ እንደነበርም አይዘነጋም። በዚያን ወቅትም የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ድሪቢን ጨምሮ በርካቶች ታስረው ነበር። ኢህአዴግ አቋሙን ለምርጫ ቀውስ ማርገቢያ በሚል ሲቀይር፣ ድርጊቱን አስቀድመው በመቃወማቸው የተገረፉ፣ የታሰሩና ከስራ እንዲሰናበቱ የተደረጉ ካሳ ሊሰጣቸው እንደሚገባ በወቅቱ ተገልጾ ነበር።
አገሪቱ ላይ ከተንሰራፋው የተለያየ ችግር ጋር ተዳምሮ በኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ እንዳይካረር ስጋት የገባቸው ክፍሎች “ኢህአዴግ ጉልበት እየተጠቀመ የሚዘራውን ቂምና ቁርሾ ካላቆመ፣ ጠብመንጃ እጄ ላይ ነው በማለት የሚፈጽመውን ግፍ በማቆም ለእርቅ ካልሰራ አሁን ባለው ሁኔታ ነገሮች ከቁጥጥር ሊወጡ” እንደሚችሉ ማስጠንቀቂያ ይሰጣሉ፤ ጂኒው አንዴ ከሳጥኑ ከወጣ በኋላ ልዩነት ሳያደርግ የሚያመጣው መዘዝ ለህወሃት/ኢህአዴግና በቅድሚያ ከዚያም ለሥርዓቱ ባለሟሎች በተዋረድ የሚባላ እሣት እንደሚሆን ታስቦ ካሁኑ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል ይላሉ።

Wednesday, April 30, 2014


ሰበር ዜና!!!

በሕገ ወጡ መጅሊስ ውስጥ መፈንቅለ ስልጣን መደረጉ

 ተነገረ!

ፕሬዚዳንቱ በሌሉበት ሥልጣናቸውን ተነጥቀዋል!


ድምፃችን ይሰማ



ረቡእ ሚያዝያ 22/2006

በዶ/ር ሽፈራው እና በደህንነት መስሪያ ቤቱ አማካኝነት የሚመሩት የአዲስ አበባ እና የአማራ መጅሊስ አመራሮች መፈንቅለ ሥልጣን ዛሬ መፈጸማቸውን የቅርብ ምንጮች ገለጹ! ይኸው መፈንቅለ ስልጣን የፌዴራል መጅሊስና የአዲስ አበባ መጅሊስን ያመሰ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ በዛሬው መፈንቅለ ስልጣን የፌዴራል መጅሊስ ፕሬዚዳንት ሸኽ ኪያር ሸኽ መሀመድ አማን፣ የፌዴራል መጅሊስ ዋና ጸሀፊ አቶ ሙሀመድ አሊ፣ ከአዲስ አበባ መጅሊስ ደግሞ ኢንጂነር ተማምና ሌላ አንድ ሀላፊ መነሳታቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ከስልጣናቸው ተነሱ የተባሉት ፕሬዝደንቱ ሸኽ ኪያር በአሁኑ ሰአት ከአገር ውጪ በሳኡዲ አረቢያ የሚገኙ መሆናቸው ታውቋል፡፡ በዛሬው መፈንቅለ ሥልጣን በሸኽ ኪያር ቦታ የኦሮሚያ ክልል ተወካዩ መተካታቸው ሲገለጽ፣ የአማራው ክልል ተወካይም የኡለማ ም/ቤቱን መረከባቸው ተሰምቷል፡፡

በዚህ ዛሬ ተጠናቀቀ በተባለው መፈንቅለ ስልጣን ታጋይ የነበሩት የትግራይ ተወካይና ም/ፕሬዝደንት ሸኽ ከድር፣ የአዲስ አበባው መጅሊስ ፕሬዝደንት ዶ/ር አህመድ እና የአማራ መጅሊስ ተወካይ አይነተኛ ሚና እንደነበራቸው የታወቀ ሲሆን ከኋላቸውም ዶ/ር ሽፈራውና የደህንነት ሀላፊዎች ሲመሩት ቆይቷል፡፡ የስልጣን ሽኩቻው ረዘም ላለ ጊዜ የቆየ ሲሆን በድሬዳዋ ከተማ በተካሄደው ጉባኤ ላይም ፈንድቶ እስከመውጣት ደርሶ ነበር፡፡ የሽኩቻው ዋነኛ ምክንያትም ከመንግስት በኩል በግዳጅ ህዝበ ሙስሊሙ ላይ ለመጫን ሲሞከር የነበረው የአህባሽ አስተሳሰብ ዳግም በህዝበ ሙስሊሙ ላይ መጫኑ እንዲቀጥል በሚፈልጉት ወገኖች እና ‹‹ህዝበ ሙስሊሙ ሲቃወመው የነበረው የግዳጅ ጠመቃ ቆሞ መጅሊሱ ሁሉንም ሙስሊም በአንድነት ሰብስቦ እና አቻችሎ መቀጠል አለበት›› በሚሉት ዛሬ ከስልጣን በተወገዱት ሀላፊዎች መካከል ያለው የአቋም ልዩነት መሆኑ ታውቋል፡፡

እስካሁን በነበረው ሂደት የመጅሊሱ ፕሬዝደንት ‹‹መጅሊሱ ህዝበ ሙስሊሙን የሚጠቅም እና በሰላም እንዲኖር የሚያደርግ እንጂ ችግር ውስጥ የሚያስገባ አካል መሆን የለበትም›› የሚል ፅኑ አቋም ይዘው የነበረ ሲሆን በሸኽ ከድር በሚመራው ቡድን እየተደረገ ያለውን ህዝበ ሙስሊሙን ዳግም ወደ ተቃውሞ ሊያስገባ የሚችል ትንኮሳ በመቃወምም ለተለያዩ የመንግስት አካላት ደብዳቤ መፃፋቸው ታውቋል፡፡

በሕገ ወጡ መጅሊስ ውስጥ ከላይ እስከታች የሚታየው የስልጣን ሽኩቻ የተቋሙን አመራር ሕገ ወጥነት አመላካች ከመሆኑም በላይ በመንግስት የተሰጠውን የቤት ስራ ለመፈጸም የተሰባሰበ ቡድን መሆኑንም ክስተቱ እማኝነት ሰጥቷል፡፡

በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችና ማብራሪያዎች በነገው እለት ይኖሩናል - ኢንሻአላህ!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!


በዋልድባ ገዳም እየተካሄደ ያለው እምነትን የማፍረስ ዘመቻ ዛሬም እንደቀጠለ በቦታው የሚገኙ መነኮሳት በምሬት ገለፁ፡፡


ድምጻችን ይሰማ ዘኦርቶዶክስ


ቀደም ሲል ወደ 20 የሚጠጉ ገዳማትን ለማፍረስ ተንቀሳቅሶ የነበረው የኢህአዴግ አፍራሽ ሀይል በመነኮሳት ፣ በባህታውያን፣… ፀሎትና በአካባቢው በሚገኙ ተቆርቋሪዎች ሲከሽፍበት የዘጉ ባህታውያንና ጨምሮ በርካቶችን በማሰር፣ በመደብደብ፣በማፈናቀልና በማንገላታት ጉዳት ማድረሱ ይታወቃል፡፡ በዚህም ያተረፈው 2ቱን ‹መሪዎችን› መለስ ዜናዊና ገ/ መድህን/ጳውሎስ ፣ በቦታው የሄዱ መሀንዲስና ሰራተኞችን፣ ጠበንጃ አንጋቾችን ጨምሮ በርካቶችን በሞት ሲነጠቅ በራሱ ላይ ከፍተኛ ችግር አድርሷል፡፡ ቃሌማ የተባለ የገዳሙ ዙሪያ በርካት ገበሬዎችን አፈናቅሎ ‹የስኳር› ተክል መዝራቱ ይታወቃል፡፡
ይሆንና በየጊዜው ኪሳራን እየተከናነበ በሀገርና በሕዝብ ላይ በደል የሚያደርሰው ኢህአዴግ በ16/ 08/ 2006 ዓ. ም በዕለተ ሀሙስ ማይ ለበጣ በተባለ ቦታ የገዳማትን ሰዎች ሰብስቦ፡-
1ኛ፡- ድልስ ቆቃ አቡነ- አረጋዊ ገዳም፣
2ኛ፡- መሀር ገፅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም፣
3ኛ፡- እጣኖ ማርያም ገዳም ፣….‹ለስኳር ልማት› እንዲፈርሱ በቀጣይ ደግሞ ማይጋባ ቅ/ ጊዮርጊስ ‹ ይነሳሉ› የሚል ሀሳብ ሲያቀርብ በርካታ ተቃውሞ ቀርቦ ከፍተኛ ውዝግብ ፈጥሯል፡፡
በመህል የሰገሰጋቸው አሰሮች የድጋፍ ድምፅ ሲያሰሙ መነኮሳትና መናንያን ተቃውሞሙን በማጠናከራቸው ለግንቦት 19 ቀን 2006 ዓ. ም ተቀጥሯል፡፡ በዚህም የዋልድባ ገዳም ተቆርቋሪ የሆናችሁ ሁሉ ድምፃችሁን አሰሙልን ሲሉ ተማፅነዋል፡፡


ለወይዘሮሪት ኢህአዴግዬ ሰው ማሰር ሻሽ ሸብ ከማድረግ እኩል ቀላል አይደለምን?! – አቤ ቶክቻዉ

ወዳጄ….
በሩቁ የምታውቀው ወዳጅህ ሲታሰር፤ አሳሪዎቹ የሚደረድሩልህ ምክንያት ትንሽ እውነት ሊኖረው ይችላል ብለህ ልታስብ ተችላለህ ከዛ አሳሪዎች መቼም ማሰር አይታክታቸውም አይደል፤ ቀረብ የሚልህ ወዳጅህን ደግሞ ያስራሉ፤ ማሰር ብቻም አይደል ያለ የሌላቸውን ምክንያቶች በቴሌቪዥን በራዲዮ አከታትለው ይነግሩሃል ይሄኔ ግራ ትጋባለህ …መንግስትን ያህል ነገር እንዲህ አይን አውጥቶ ሊዋሽ ይችላል….. ወይስ ወዳጄን በቀጡ አላውቀውም ነበር ብለህ ይምታታብሃል…
የኔ ጌታ አሳሪ ጠዋት ቀበቶውን ካሰረ ሰዓት አንስቶ ሙሉውን ቀን፤ “ደግሞ ማንን ልሰር….” ሲል ነው የሚወለው። እና እያለ፣ እያለ ከራስህ በላይ አውቀዋለው የምትለውን ወዳጅህን ወይም እራስህን ጥርቅም አድርጎ ያስራል። ይሄኔ የፈለግ ምክንያት ቢደረደርልህ አሳሪውን ልታምን እንደማትችል የታወቀ ነው ሀቁ ያለው ራስህ ጋ ነዋ!
እናም ወዳጄ…
በተለይ እንደ ኢህአዴግ ያለ የማሰር ሱስ ያለበት አሳሪ በሩቁ የምታውቃቸውንም በቅርብ የምታውቃቸውንም አስሮ ምክንያት ሲደረድር ወዳጆችህን አተጠራጠር እውነቴን ነው የምልህ መንግስታችን ሰዎችን ሲያስር ጥጃ የማሰር ያክል አይጨንቀውም። ለዚህ ደግሞ አጥጋቢ ምክንያት ሲፈልግ አየገኝም፤ በቃ የአይንህ ቀለም ካላማረው ያስርሃል።
የ ዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችን የማውቃቸው ማንም ሰው የታሰረ እነደሆነ መዝገብ አገላብጠው መታሰሩ ከህግ አንጻር፣ ከህገ መንግስት አንጻር፣ ከሞራል አንጻር፤ እያሉ የህሊና ፍርድ ሲሰጡ ነው። ሙስሊም ሳይሉ ክርስቲያን ሳይሉ ኦሮሞ ሳይሉ ጋምቤላ ሳይሉ ያለ ለዩነት ጆሯቸው የደረስ አይናቸው ያየውን ኢፍትሃዊነት ሲያወግዙ ነው። ደግሞ ሲያውግዙ ብቻ አይምሰልህ መንግስት የሚሰራቸው መልካም ነገሮችም እውቅና ሊሰጠው ይገባል፤ ጽንፈኛ መሆን ተገቢ አይደልም ሲሉም ይውቅሱሃል።
ዛሬ መንግስት እነዚህን ወጣቶችን ሰባስቦ አስሯቸዋል። (ለወይዘሮሪት ኢህአዴግዬ ሰው ማሰር ሻሽ ሸብ ከማድረግ እኩል ቀላል ነው (በሌላ ቅንፍ ኢህአዴግዬን ወይዘሮሪት ያልኩታ ታግባ አታግባ በቀጡ ሰላላወቅሁ ነው፤ ግራ ስታገባን ግን በድንብ አውቃታለሁ… ሃሃ))
እኔ በአስሩም ጣቴ እፈርማለሁ፤ ዘጠኙም ጋዜጠኞች እና አስተያየት ሰጪዎች የታሰሩት እንደ ሰው በማሰባቸው እና በሀገራችን ጉዳይ ያገባናል በማለታቸው ብቻ ነው!
እንደዚህ የምልህ መንግስቴ ከሀገሬ አሯሩጦ ስላስወጣኝ ቂም ይዤ አለመሆኑን ድንጋይ ነክሼ እምልልሃለሁ!