በዋልድባ ገዳም እየተካሄደ ያለው እምነትን የማፍረስ ዘመቻ ዛሬም እንደቀጠለ በቦታው የሚገኙ መነኮሳት በምሬት ገለፁ፡፡
ድምጻችን ይሰማ ዘኦርቶዶክስ
ቀደም ሲል ወደ 20 የሚጠጉ ገዳማትን ለማፍረስ ተንቀሳቅሶ የነበረው የኢህአዴግ አፍራሽ ሀይል በመነኮሳት ፣ በባህታውያን፣… ፀሎትና በአካባቢው በሚገኙ ተቆርቋሪዎች ሲከሽፍበት የዘጉ ባህታውያንና ጨምሮ በርካቶችን በማሰር፣ በመደብደብ፣በማፈናቀልና በማንገላታት ጉዳት ማድረሱ ይታወቃል፡፡ በዚህም ያተረፈው 2ቱን ‹መሪዎችን› መለስ ዜናዊና ገ/ መድህን/ጳውሎስ ፣ በቦታው የሄዱ መሀንዲስና ሰራተኞችን፣ ጠበንጃ አንጋቾችን ጨምሮ በርካቶችን በሞት ሲነጠቅ በራሱ ላይ ከፍተኛ ችግር አድርሷል፡፡ ቃሌማ የተባለ የገዳሙ ዙሪያ በርካት ገበሬዎችን አፈናቅሎ ‹የስኳር› ተክል መዝራቱ ይታወቃል፡፡
ይሆንና በየጊዜው ኪሳራን እየተከናነበ በሀገርና በሕዝብ ላይ በደል የሚያደርሰው ኢህአዴግ በ16/ 08/ 2006 ዓ. ም በዕለተ ሀሙስ ማይ ለበጣ በተባለ ቦታ የገዳማትን ሰዎች ሰብስቦ፡-
1ኛ፡- ድልስ ቆቃ አቡነ- አረጋዊ ገዳም፣
2ኛ፡- መሀር ገፅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም፣
3ኛ፡- እጣኖ ማርያም ገዳም ፣….‹ለስኳር ልማት› እንዲፈርሱ በቀጣይ ደግሞ ማይጋባ ቅ/ ጊዮርጊስ ‹ ይነሳሉ› የሚል ሀሳብ ሲያቀርብ በርካታ ተቃውሞ ቀርቦ ከፍተኛ ውዝግብ ፈጥሯል፡፡
1ኛ፡- ድልስ ቆቃ አቡነ- አረጋዊ ገዳም፣
2ኛ፡- መሀር ገፅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም፣
3ኛ፡- እጣኖ ማርያም ገዳም ፣….‹ለስኳር ልማት› እንዲፈርሱ በቀጣይ ደግሞ ማይጋባ ቅ/ ጊዮርጊስ ‹ ይነሳሉ› የሚል ሀሳብ ሲያቀርብ በርካታ ተቃውሞ ቀርቦ ከፍተኛ ውዝግብ ፈጥሯል፡፡
በመህል የሰገሰጋቸው አሰሮች የድጋፍ ድምፅ ሲያሰሙ መነኮሳትና መናንያን ተቃውሞሙን በማጠናከራቸው ለግንቦት 19 ቀን 2006 ዓ. ም ተቀጥሯል፡፡ በዚህም የዋልድባ ገዳም ተቆርቋሪ የሆናችሁ ሁሉ ድምፃችሁን አሰሙልን ሲሉ ተማፅነዋል፡፡
No comments:
Post a Comment