ዝቶ በመስጠትና የድምፅ መልዕክቱን በማስደመጥ ኃላፊነታችንን እንወጣ!!!
ሙሉ ፅሁፉን ከዚህ በፊት ፖስት ከተደረገው ላይ ማግኘት ይችላሉ . . . .
''ምድር ህላዌዋ ከተቦካበት ቅፅበት አንስቶ በለውጥ ምህዋር ላይ እየተሸከረከረች ትገኛለች፡፡ ቀኑ ሰዐቱን ጠብቆ ሲመሽ ብርሀን በጨለማ ይለዋጣል፡፡ ምሽቱ ተራውን ለቀን ሲያስረክብ ደግሞ ጨለማው በብርሃን ይለወጣል፡፡ ምድር ሁሌም በለውጥ ሀዲድ ላይ ትከንፋለች፡፡ ዛሬ ከትላንት፣ ነገም ከዛሬ ለውጥን ይቀባበላሉ፡፡ የሰው ልጅ የህይወት ዑደት ስለ ለውጥ ተፈጥሮዊነት አይነተኛ ማሳያ ነው፡፡ ከአንቀልባ እስከ ከፈን በሚዘረጋው የህይወት ጅረት የሰው ልጅ ሲፈስ በበርካታ የለውጥ ድልድዮች ስር ያልፋል፡፡ . . . ''
''ላለፉት ሁለት አመታት አንግበን የተነሳናቸው ሶስቱ የመብት ጥያቄዎች ምላሽ ያገኙ ዘንድ ደከመን ሰለቸን ሳንል በትዕግስት እየታገልን ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡ እነዚሁ ያሳለፍናቸው የትግል አመታት ሂደታቸው ፍፁም ያማረ ቢሆንም ሶስቱን ጥያቄዎች ማስመለስን ገደብ አድርገን የተጓዝናቸው የትግል ጎዳናዎች ግን የምንፈልገው ቦታ ሊያደርሱን አልቻሉም፡፡ መንግስትም ጉዳዩን አጢኖ እልባት እንዲያገኝ ከመትጋት ይልቅ በአጉል ስም ማጥፋት ተጠምዶ ትግሉን በሀይል ለማስቆም እየባተለ ይገኛል፡፡ሙስሊሙ ህብረተሰብ የሀይል እርምጃው ሳይገታው ‹‹ጥያቄዎቹ አለተመለሱም›› ሲል ትግሉን ቢቀጥልም የመንግስት አፀፋ ግን ለሞት እና ለጅምላ እስር ዳርጎታል፡፡ ቀን በቀን በተተካ ቁጥር የመንግስት እምቢተኝነትና የሚወሰደው እርምጃ ሲጨምር እንጂ ሲቀንስ አልታየም፡፡ ይህም ሆኖ ግን ትግሉ ከተጀመረበት ቅፅበት አንስቶ ባሳለፋቸው ሂደቶች የተከፈሉት ከፍተኛ መስዕዋትነቶች በርካታ የድል ፍሬዎችንም አስገኝተዋል፡፡ . . . ''
''የኢትዮጲያ ሙስሊም በእምነቱ ላይ የተቃጣውን የአስተሳሰብና የመብት ጥሰት ዘመቻ ለመመከት፣ አስተሳሰቡን በኢስላማዊ አስተሳሰብ ለማረቅ፣ የሕግ ጥሰቱ በህግ ማእቀፍ ዕልባት ያገኝ ዘንድ ስላማዊ ትግል ሲጀምር መሪዎችን ከመፍጠሩም በላይ የተመሪነትን ስርዓት ለሀገራችን ታሪክ አዲስ በሆነ መልኩ ማሳየትና ማስተዋወቅ ችሏል፡፡ ሕዝቡ የፈጠራቸውን መሪዎች ያለጥርጥር ተከትሏል፡፡ ትዕዛዛቸውን ያለ ፍርሀት ተግብሯል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ በባለቤትነት በሚመራው በዚሁ የመብት ማስከበር ስላማዊ ትግል ሂደት ውስጥ ልክ እንደማንኛውም ትግል ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፏል፡፡ በርካታ መስዕዋትነት ከፍሏል፤ እየከፈለም ይገኛል፡፡ እስከ ድል ጫፍ በተዘረጋው የትግል ድልድይ ሲያልፍ እስራት፣ ድበደባ፣ ዛቻ፣ ማስፈራሪያ፣ ስም ማጥፋትና መገለል ደርሶበታል፡፡ እነዚህ የትግል ገፅታዎች ህዝበ ሙስሊሙ በትግሉ መባቻ ላይ ከነበረው ቁመና ከፍ ያለ ተነሳሽነትና ፅናት ላይ እንዲገኝ አስችለውታል፡፡ በዚህም የአስተሳሰብ እመርታና የባህሪ ለውጥ ከማምጣቱም ባሻገር በትግሉ ሂደትም ላይ ተገቢ የሆነ የለውጥ ፍላጎት አሳድሮበታል፡፡. . .''
''በሃምሌ 2003 የአህባሽ ጠመቃ ዋነኛ መንስኤነት የተጀመረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን የመብት ማስከበር ትግል ትላልቅ እርከኖችን አልፎ መጥቷል፡፡ አሁን ወደ ቀጣዩ እርከን የሚሸጋገርበት ወሳኝ ወቅት ላይ ይገኛል፡፡ እስካሁን በነበረው ሂደት ትግሉ ይዞት ከተነሳቸው ሶስት ጥያቄዎች አለመመለስ ውጭ እጅግ ውጤታማ ሂደት ነበር፡፡ ምናልባት ጥያቄዎቹ ቢመለሱ ሊሰጡት ከሚችሉት ጥቅም በላይ ሌሎች ትልልቅ ፋይዳዎችን ለኡማው አበርክቷል፡፡ ከውጤቶቹ አንዱ ደግሞ ህዝባችን መብታችንን ማስከበር እና ከውስጥ ጉዳያችን የመንግስትን ጣልቃ-ገብ እጆች ማስወጣት ጊዜ ሊሰጠው እንደማይገባ በይፋ መናገር የሚችልበት ደረጃ ላይ መድረሱ ነው፡፡. . . ''