የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የትግል መሪ የሆነው ''ድምፃችን ይሰማ'' የፌስቡክ ፔጅ
ለአዲሱ የትግል ምዕራፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንቅስቃሴውን ጀመረ!!!
''ድምፃችን ይሰማ'' አዲሱን የትግል ምዕራፍ አስመልክቶ ህዝበ ሙስሊሙ የጋራ
ግንዛቤ ይኖረው ዘንድ የተለያዩ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ላይ ይገኛል::
መልዕክት ቁጥር 3 እነሆ!
#EthioMuslimStruggle
አዲሱን የትግል ምእራፍ አስመልክቶ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖረን የተላለፈ መልእክት - ቁጥር 3
የህዝቡን የለውጥ ፍላጎት መረዳት ተገቢ ነው!
ሰኞ ሚያዝያ 20/2006
የኢትዮጲያ ሙስሊም በእምነቱ ላይ የተቃጣውን የአስተሳሰብና የመብት ጥሰት ዘመቻ ለመመከት፣ አስተሳሰቡን በኢስላማዊ አስተሳሰብ ለማረቅ፣ የሕግ ጥሰቱ በህግ ማእቀፍ ዕልባት ያገኝ ዘንድ ስላማዊ ትግል ሲጀምር መሪዎችን ከመፍጠሩም በላይ የተመሪነትን ስርዓት ለሀገራችን ታሪክ አዲስ በሆነ መልኩ ማሳየትና ማስተዋወቅ ችሏል፡፡ ሕዝቡ የፈጠራቸውን መሪዎች ያለጥርጥር ተከትሏል፡፡ ትዕዛዛቸውን ያለ ፍርሀት ተግብሯል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ በባለቤትነት በሚመራው በዚሁ የመብት ማስከበር ስላማዊ ትግል ሂደት ውስጥ ልክ እንደማንኛውም ትግል ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፏል፡፡ በርካታ መስዕዋትነት ከፍሏል፤ እየከፈለም ይገኛል፡፡ እስከ ድል ጫፍ በተዘረጋው የትግል ድልድይ ሲያልፍ እስራት፣ ድበደባ፣ ዛቻ፣ ማስፈራሪያ፣ ስም ማጥፋትና መገለል ደርሶበታል፡፡ እነዚህ የትግል ገፅታዎች ህዝበ ሙስሊሙ በትግሉ መባቻ ላይ ከነበረው ቁመና ከፍ ያለ ተነሳሽነትና ፅናት ላይ እንዲገኝ አስችለውታል፡፡ በዚህም የአስተሳሰብ እመርታና የባህሪ ለውጥ ከማምጣቱም ባሻገር በትግሉ ሂደትም ላይ ተገቢ የሆነ የለውጥ ፍላጎት አሳድሮበታል፡፡
ሕዝቡ በጊዜ ሂደት ይፈታሉ በሚል እሳቤ በይደር ያቆያቸው ሌሎች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊም ሆነ ተያያዥ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ስር እየሰደዱ ከመሆናቸውም ባሻገር በገደብ የተሰጡትን መሰረታዊ መብቶችም መልሶ የመንጠቅ ስራ እየተሰራበት ይገኛል፡፡ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬም ከማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ብሎም የአንድን ሀገር እውቀት በማምረት መፃኢ እድሏን ከሚወስነው የትምህርት መድረክ በስልት እየተገፉ ይገኛሉ፡፡ ይህም ሙስሊሙ እጁን አጣጥፎ እንዲቀመጥ ሳይሆን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነቱን በሚያረጋግጡ መርሆች ላይ የተመሰረተ ሰፊ ትግል እንዲያደርግ ገፊ ከመሆኑም በላይ በፅኑ ተነሳሽነት የተወለደው ይኸው ግለት የለውጥ ፍላጎቱን አገንፍሎታል፡፡ የችግሮቹ ብዛትና ያለንበት ሁኔታ ሚዛን አለመድፋቱ የትግል ተሀድሶን እንዲሻ አስገድዶታል፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ በሶስቱ ጥያቄዎች ሳይገደብ የመንግስትን ሴራዎችና ቀጣይ ፈተናዎችን ግምት ውስጥ በሚያስገባ መልኩ ለዘላቂና ሁለንተናዊ መፍትሄ እንዲንቀሳቀስ የማንቃት ስራ ለመስራት የተፈጠረው የለውጥ ፍላጎት አጋዥ እንደሚሆን ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ይህንኑ በለውጥ ፍላጎት የተሞላ የህዝቡን ስሜት በመረዳት፣ የወቅቱን ተጨባጭ እና የማስፈፀም አቅም ከግምት ያስገባ፣ በትግሉ ሂደት የተፈጠረውን ህዝባዊ ተነሳሽነትና የአንድነት ስሜት እንደለም አፈር በመጠቀም ዘርፈ ብዙ ችግሮቹን ለመፍታት የሚችልበትን የተሀድሶ አቅጣጫ መንደፉ ተገቢ ሆኗል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ የትግሉ ባለቤት፣ የመሪዎቹም መሪ በመሆኑ ቀጣይ የትግሉን ሂደትና የተሀድሶ አድማስ የሚወሰነው የህዝበ ሙስሊሙን የልብ ትርታ፣ ስሜትና የለውጥ ፍላጎት በመንተራስ ነው፡፡ ሕዝቡ በአጠቃላይ ሂደቱ አንድ እርምጃ ወደፊት መጓዝ ይፈልጋል፡፡ ለዚህ ደግሞ የራስ ተነሳሽነት፣ አርቆ አሳቢነትና ቁርጠኝነት ሁነኛ ግብአቶች ይሆናሉ፡፡ ራሳችንን ለተሻለ ድል ከፍ እናድርግ፡፡
የትግል አቅጣጫ ማስገንዘቢያ መልእክቱን የድምጽ ትረካ ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ፡-
http://goo.gl/zqdaiz
ትግላችን እስከድል ደጃፎች ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

No comments:
Post a Comment